Boru Meda Hospital

ትራኮማን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ሙያዊና ስልታዊ መመሪያ ለመስጠት በጉዳዩ ላይ የሚሰሩ የአለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ድርጅቶች እንዲሁም ገለልተኛና አለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ባለሙያዎችን ያቀፈ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የጤና የሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ሌሊሳ አማኑኤል ኢትዮጵያ የትራኮማ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና ለማጥፋት በሽታው በብዛት በሚታይባቸው ክልሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ ምርመራና ህክምና እየተሰጠ መሆኑን በመጥቀስ አዳዲስ ስልቶች እና ቅንጅታዊ የአገልግሎት አሰጣጥን መሰረት ያደረገ ትግበራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በሽታውን በ2030 እ.ኤ.አ የህብረተሰብ ጤና ችግር የማይሆን ደረጃ ለማድረስ ጤና ሚኒስቴር ስትራቴጂ ቀርፆ ከክልል ጤና ቢሮዎች፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መለከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ ትኩረት የሚሹ ሃሩራማ በሽታዎች ዴስክ ሃላፊ አቶ ተስፋሁን ቢሻው በበኩላቸው የማህበረሰብ አቀፍ የመድሃኒት እደላ ለሁሉም ከፍተኛ ስርጭት ለሚታይባቸው ወረዳዎች በመስጠት፣ የአይን ቆብ መቀልበስ የታየባቸውን ህሙማን ማስተካከያ ቀላል ቀዶ ህክምና በማድረግ እና የአካባቢና የግል ንፅህና አጠባበቅ እንዲሻሻል ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር በመቀናጀት እተሰራ መሆኑ ጠቅሰው ስርጭቱን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል።

በጉባኤው ተሳታፊ የነበሩ የተለያዩ አጋር እና ለጋሽ ድርጅቶች ይህ በሽታ በብዙ የአለም አገራት በእጅጉ እቀነሰ መሆኑን ጠቅሰው በኢትዮጵያም ለተነደፈዉ ስትራቴጂ ስኬት ድጋፍ እንደሚያደርጉና ከጤና ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *