Boru Meda Hospital

ህዳር 8/ 2018
ቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል
ደሴ
በአብክመ ጤና ቢሮ አማካኝነት በደሴ ከተማ በቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የሚገኘውና የግንባታ ሥራው እየተጠናቀቀ ያለው በተመላላሽና በተኝቶ ህክምና ለስነ አዕምሮ እና ለሱስ ማገገሚያ ህክምና እንዲሁም የምርምርና የማስተማሪያ አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ የሚጠበቀው የህክምና ማዕከል የግንባታ ሥራው እየተጠናቀቀ በመሆኑ ሥራ ለማስጀመር በሆስፒታሉ መሠራት የሚገባቸው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዙሪያ ከባለሙያዎቹ ጋር ሰፊ ውይይት አካሂዷል ።
የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ባሉት የስነ አዕምሮ ህክምና ባለሙያዎች ትጋትና በማኔጅመንቱ ጥረት ባሉት ክፍሎች እስከአሁን ለበርካታ ህሙማን እገዛ ያደረገ ሲሆን በቅርቡ ሥራ በሚጀምረው ዘመናዊ የህክምና ማዕከሉ ጥራት ያለው እና የላቀ ህክምና በመስጠት በዘርፉ የልህቀት ማዕከል አቅዶ እየሠራ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *