Boru Meda Hospital

የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል የዓይን እንባ ቱቦ መዘጋት ችግር ላለባቸው ታካሚዎች ነጻ የቀዶ ህክምና አገልግሎት እያከናወነ ነው

የካቲት27/2018 ዓ.ም

ቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል

ደሴ

የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ኦፕሬሽን ኢትዮጵያ ከሚባል ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከየካቲት 26 ቀን/2018 ዓ ም ጀምሮ ለሰባት ቀናት የእንባ ቱቦ መዘጋት ችግር ላለባቸው ታካሚዎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት እያከናወነ በነጻ እየሰጠ ሲሆን በዚህ የህክምና አገልግሎት እስከ ሦስት መቶ የሚሆኑ ታካሚዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

እንደሚታወቀው ሆስፒታሉ በመደበኛ ከሚሰጠው የዓይን ህክምና አገልግሎት በተጨማሪ በዘመናዊ ህክምና መሣሪያዎች በመታገዝ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በየዓመቱ እስከ ስምንት ሽህ ለሚሆኑ ታካሚዎች ለዓይን ሞራ ግርዶሽ፣ ለእንባ ቱቦ መዘጋት እና ለዓይን ቆብ ፀጉር መቀልበስ ችግሮች ዘመቻ በማድረግና ነፃ ህክምና በመስጠት ለበርካቶች የዓይን ብርሃናቸውን እየመለሰ ይገኛል

ቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል

ለበለጠ መረጃ ዌብ ሳይታችን(https://www.borumedahospital.gov.et/) ፡ ቴሌግራም(https://t.me/BoruMeda_G_Hospital) እና የፌስ ቡክ ገጻችን ይጎብኙ እንዲሁም በ8352 በነጻ የስልክ ጥሪ መረጃ ያግኙ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *