የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ከመደበኛ የዓይን ህክምና አገልግሎቱ ባሻገር በዓመት ከሁለት እስከ ሦስት ጊዜ ዘመቻ በማድረግ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ላለባቸው በርካታ ወገኖቻችን ነፃ የቀዶ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ህሙማን የዓይን ብርሃናቸው እንዲመለስ እያደረገ ይገኛል ።
በዚህም መሠረት ኪዩር ብላይንድነስ ከሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በተባበር ከ 24/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 29/02/2018 ዓ.ም ድረስ የቆየ ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት በደ/ወሎ እና አጎራባች ዞኖች ለሚገኙ በርካታ ተገልጋዮች ተሰቷል።
ቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል
ደሴ


