የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ከመደበኛ የዓይን ህክምና አገልግሎቱ ባሻገር በዓመት ከሁለት እስከ ሦስት ጊዜ ዘመቻ በማድረግ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ላለባቸው በርካታ ወገኖቻችን ነፃ የቀዶ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ህሙማን የዓይን ብርሃናቸው እንዲመለስ እያደረገ ይገኛል ።
የዚህ የህክምና ዘመቻ ለየት የሚደረገው ከመቼውም በላይ ለማህበረሰባችን ተደራሽ ለማድረግ እና ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የደ/ወሎ ዞን አስተዳደር ሁሉም በየደረጃው ትኩረት የሰጡት መሆኑ፣ የሆ/ሉ ቦርድ እና ማነጅመንት አባላት፡ ሌት ከቀን ሲከታተለው የነበረ መሆኑ ፣ በተለያዩ ተቌማት የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች የታካሚዎችን ህመም ለመለየትየተሳተፋ መሆኑ ፣ ለምሳሌ ያክል ለገሂዳ ወረዳ ህሙማንን ከላዩ በኋላ የህሙማንን እንግልት ለመቀነስ መጓጓዣ በማዘጋጃት እና ከባለሙያዎች ጋር ጠርንፈው ይዘው የመጡበት፣ ህክምናው ከጨረሱ በሗላም ወደ ቀያቸው በሰላም የመለሱበት ጥሩ ተሞክሮ የተቀመረበት ዘመቻ ነበር። እንዲሁም ዘመቻው የክልሉ ጤና ቢሮ አመራሮች እና የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በአካል ተገኝተው የጐበኙት ሲሆን ሆስፒታሉ ጥራቱን የጠበቀ የአይን ህክምና እየሰጠ መሆኑን ታዝበው ይህን ለማስቀጠል እና የአይን ህክምናው እንደጠናከር ለማደረግ እገዛቸው እንደማይለይ ቃል ገብተዋል።
በዚህም መሠረት ኪዩር ብላይንድነስ ከሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በተባበር ከ24/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 29/02/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት በደ/ወሎ እና አጎራባች ዞኖች ለሚገኙ በርካታ ተገልጋዮች ለመስጠት ታቅዶ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡ ።
ዓይነ ስውርነት መቀነስ ድህነትን መቀነስ ነው!!!
30 /02/2018
ቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል
ደሴ




