ህዳር 11/2018
ቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል
ደሴ
የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ በአዲስ መልኩ በተቀየረው የአይ ኤስ ኦ 2022 መመዘኛ መስፈርት መሠረት በቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ላቦራቶሪ ክፍል የመጀመሪያ ዙር ምልከታ እና ድጋፋዊ ጉብኝት ያካሄደ ሲሆን ድጋፉን ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች አቶ አበበ ኢያሱ እና አቶ አሰፋ ምሳዬ ከመስፈርቱ አንፃር የተሰሩ ጠንካራ ጎኖችን እንዲቀጥሉ አበረታትተው ቀሪ ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈፅመው ወደ እውቅና እንደሚገባ በመጠቆም ግብረ መልስ ሰጥተዋል።
ግብረ መልሱን የተቀበሉት የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ፣ሜዲካል ዳይሬክተር ፣ የላቦራቶሪ ክፍሉ ኃላፊና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው ክፍሎች አስተባባሪዎች ሲሆኑ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ተበጀ የላቦራቶሪ ክፍሉን ለማጠናከርና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በዚህ ዓመት በማኔጅመንቱ በትኩረት እንደተያዘ ገልፀዋል ።
እንደሚታወቀው የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል
ላቦራቶሪ ክፍል የማይክሮባዮሎጂ አገልግሎት ያለውና ቀደም ሲልም በርካታ ልምዶች የተቀመሩበት ሲሆን አሁን ላይም ለበርካታ ጤና ጣቢያዎች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።



